Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hostingየኮሚሽነሩ መልዕክት

በአገራች ባለፉት አስርት ዓመታት የታየው አበረታች የኢኮኖሚ እድገት ለውጥ የበለጠ እንዲፋጠንና አገራችን የነደፈችውን ሁለተኛው የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሳካ ሁሉም የኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ መስኮቻችን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዕውቀትና ክህሎት መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡

አገራችን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የማታደርገውን የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ሽግግር እንዲሳካ ኮሚሽናችን ከተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት አንጻር በክልላችን የምርትና የአገልግሎት ጥራትን ለማዘመን፣ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከእነዚህም መካከል ለመጥቀስ ያህል ተቋማችን ቅድሚያ በመስጠት የቴክኖሎጂውን አብይ ተዋናይ ማህበረሰብ በሳይንሳዊ እውቀትና በፈጠራ ክህሎት ለማጎልበት በሰው ሃይል ልማት እንዲሁም በምርምርና ቴክኖሎጂ መረጣ ላይ ሰፊ ስራዎችን ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካትና በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት የሁሉንም አካል ርብርብና ቅንጅታዊ አሰራር ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ሁላችንም በመቀናጀት አስፈላጊውን ጥረት እንድናደርግ አሳስባለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ዶ/ር ሰብስበው አጥቃው

ኮሚሽነር

 

የሩዝ ማጨጃ ቴክኖሎጂዎች ተዋወቁ፡፡


በአብክመ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን በአግሮ ቢግ የገንዘብ ድጋፍ ከውጭ ያስመጣቸውን የሩዝ ማጨጃ ማሽኖች ለአርሶ አደሮች አስተዋወቀ፡፡ ህዳር 19/2012 ዓ.ም በወረታ ከተማ በሚገኘው የሩዝ ምርምር ማዕከል በተካሄደው ሙከራ ከ750 በላይ የሚሆኑ በፎገራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች ተሳትፈውበታል፡፡

ማሽኖቹ ሩዝ በማጨድ ለአርሶ አደሮች የተዋወቁ ሲሆን በድህረ ምርት ወቅት የሚደርሰውን የምርት ብክነት ለመቀነስ ከሚኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ጉልበትና ጊዜ በመቆጠብ በኩል የሚኖራቸው ሚና የጎላ መሆኑን ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡  በኮሚሽኑ የተዋወቁት ሁለት የሩዝ ማጨጃ ማሽኖች በሞተር ሃይል በእጅ እየተገፋ የሚንቀሳቀስና በሰው ትክሻ ታዝሎ የሚሰራ ሲሆኑ ወደፊት በኢንተርፕራይዞች እየተባዙ ለአርሶ አደሩ እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡

ተሳታፊ አርሶ አደሮቹ ማሽኖችን በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡


የሳይንስ ካፌ ተመረቀ።
===============
በባህር ዳር ከተማ በኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገነባው የሳይንስ ካፌ ጥቅምት 22/2012 ዓ.ም ተመረቀ፡፡ በባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ማዕከል የተገነባውን የሳይንስ ካፌ መርቀው የከፈቱት የከፈቱት የኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር አህመዲን እና የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር  የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ አምሳል ሲሆኑ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

የሳይንስ ካፌዎች ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቶች በአንድ ማዕከል የመሰብሰቢያ መድረክ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀትን የሚቀስሙበት፣ የሚወያዩበት፣ የሚሰለጥኑበት፣ ሳይንሳዊ አስተሳሰብና የፈጠራ ባሕል በወጣቱና በመላው ሕብረሰብ እንዲሰርጽና እንዲዳብር በማድረግ ለዘላቂ አገራዊ ዕድገት ጉልህ ፋይዳ እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚገነቡ ማዕከላት መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በኢፌዲሪ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተገነባው ከባህር ዳር የሳይንስ ካፌ በተጨማሪ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጀት በደሴ፣ ደብረ ብርሀንና ጎንደር ከተሞች ተጨማሪ የሳይንስ ካፌዎች በክልሉ በመገንባት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የባህር ዳር ሳይንስ ካፌ በውስጡ በተለያዩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ ውይይት የሚደረግበት መለስተኛ የመወያያ ክፍል፣ የካፊቴሪያ አገልግሎት፣ የዲጅታልና ፊዚካል ቤተ-መጽሀፍትና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ክፍሎችን ያካተተ ሲሆን የግንባታ ስራውና ቁሳቁስ ማሟላት ተግባራት ከተጠናቀቁ በኋላ አገልግሎት እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡

  
We have 10 guests online

Multidimensional News

      

Acquired immune deficiency syndrome (AIDS) is known to be caused by  Humanimmuno virus (HIV).

     It is a highly spreading virus through out the world.

   The virus is believed to be found only in human beings and transmitted from person to person by    unprotected sexual intercourse, mother to child during pregnancy and delivery and sharing sharp materials, the virus basically attacks immune cells and CD4 cells.

read more ...