Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting


Amhara Science, Technology and Information Communication Commission::Home


የኮሚሽነሩ መልዕክት

 

በአገራች ባለፉት አስርት ዓመታት የታየው አበረታች የኢኮኖሚ እድገት ለውጥ የበለጠ እንዲፋጠንና አገራችን የነደፈችውን ሁለተኛው የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሳካ ሁሉም የኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ መስኮቻችን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ዕውቀትና ክህሎት መደገፍ ይኖርባቸዋል፡፡

አገራችን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የማታደርገውን የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ሽግግር እንዲሳካ ኮሚሽናችን ከተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት አንጻር በክልላችን የምርትና የአገልግሎት ጥራትን ለማዘመን፣ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ጠንክሮ እየሰራ ይገኛል፡፡

ከእነዚህም መካከል ለመጥቀስ ያህል ተቋማችን ቅድሚያ በመስጠት የቴክኖሎጂውን አብይ ተዋናይ ማህበረሰብ በሳይንሳዊ እውቀትና በፈጠራ ክህሎት ለማጎልበት በሰው ሃይል ልማት እንዲሁም በምርምርና ቴክኖሎጂ መረጣ ላይ ሰፊ ስራዎችን ለመስራት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካትና በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት የሁሉንም አካል ርብርብና ቅንጅታዊ አሰራር ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ሁላችንም በመቀናጀት አስፈላጊውን ጥረት እንድናደርግ አሳስባለሁ፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ዶ/ር ሰብስበው አጥቃው

ኮሚሽነር

ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

====================================

‘’ሃገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና’’ በሚል መሪ ሃሳብ የአብክመ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኮሚሽን ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ህዳር 28/2011 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ውይይት አካሄዱ፡፡ የመወያያ ሰነዱ በኮሚሽኑ ም/ኮሚሽነር አቶ መላኩ ጥላሁን የቀረበ ሲሆን አገራዊ ለውጡን የተመለከቱ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶክተር ሰብስበው አጥቃው ለሰራተኞች እንደገለፁት የኮሚሽኑ ተግባር በክልሉ የሚገኙ ሁሉንም ተቋሞች ተግባር የሚነካ በመሆኑ ስራው ልዩ ትኩረት የሚያስፈልገውና በተጣለብን ሃላፊነት ልክ መስራትና ለውጡን በተገቢው መንገድ መደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡

በዚሁ መድረክ በኮሚሽኑ የኤሌክትሮኒክስ መንግስት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች የተለሙ ሲስተሞች ቀርበው በተሳታፊዎቹ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ሲስተሞቹ ስራን ቀላልና ቀልጣፋ እንደሚያደርጉ ባለሙያዎች አመልክተዋል፡፡

የተዘጋጁት ሲስተሞቹም ኮምፕሌን ማኔጅመንት ሲስተም፣ ዲጂታል ላይብራሪ፣ አቴንዳንስ ማኔጅመንት ሲስተም እና ዶኩመንት ማኔጅመንት ሲስተሞች ናቸው፡፡

እንደ ዶክተር ሰብስበው ገለፃ ሲስተሞቹን በኮሚሽኑ ደረጃ ጥቅም ላይ በማዋል በሂደት እንዲሻሻሉና ውጤታቸው እየታየ ሌሎች የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶችም እንዲጠቀሙበት ይደረጋል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

የዳሰሳ ጥናት ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

= = = = = = = = = = = = =

በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተካሄደ የሰራተኞች የስራ ቦታ ላይ አመለካከት የዳሰሳ ጥናት ተጠናቆ በተገኘው ውጤት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

ህዳር 28/2011 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ በተካሄደው የኮሚሽኑ ሰራተኞች ውይይት ላይ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተሩ አቶ ጌታነህ አያሌው የዳሰሳ ጥናቱን ውጤት ለአመራሮቹና ሰራተኞች አቅርበዋል፡፡

እንደዳይሬክተሩ ገለፃ የዳሰሳ ጥናቱ የሰራተኞችን የስራ ቦታ ላይ አመለካከት በመዳሰስ ክፍተቶችን የለየ፣ የአመራሮችን ውሳኔ የመስጠት ሂደት ሊያግዝ የሚችልና በቀጣይ ሌሎች ጥናቶችን ለማድረግ መነሻ መሆን የሚችል ነው ብለዋል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን ከተቋማዊ እይታ፣ ከአመራር ድጋፍ እይታ እና ከልዩ ልዩ ጉዳዮች አንጻር ተተንትኖ የቀረበ ሲሆን መጠናዊ የአጠናን ዘዴን ተጠቅሟል፤ የዳሰሳ ጥናቱ ሰራተኞቹና አመራሮቹ በአሉታ ላነሷቸው አመለካከቶች ምክረ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን በአምስት ምዕራፎች ተዋቅሮ የቀረበ ነው፡፡

 

በቀረበው የዳሰሳ ጥናት ውጤት ላይ የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች ተወያይተውበታል፡፡


ማስታወቂያ

 

 
About the Service Delivery
 
We have 1 guest online

Multidimensional News

      

Acquired immune deficiency syndrome (AIDS) is known to be caused by  Humanimmuno virus (HIV).

     It is a highly spreading virus through out the world.

   The virus is believed to be found only in human beings and transmitted from person to person by    unprotected sexual intercourse, mother to child during pregnancy and delivery and sharing sharp materials, the virus basically attacks immune cells and CD4 cells.

read more ...